Discoverትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle
ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle
Claim Ownership

ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle

Author: DW

Subscribed: 3Played: 94
Share

Description

አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።
571 Episodes
Reverse
30 ሚሊዮን ነዋሪ ያላት ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ኮትዲቫር ቅዳሜ፤ ጥቅምት 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አካሂዳለች ። ለአራተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራ ያሸንፋሉ የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቷል ። የ83 ዓመቱ አዛውንት የአገሪቱ ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራን ጨምሮ አምስት ተፎካካሪዎች ለፕሬዚደንትነት ተፎካክረዋል
ስደተኞችን ከመስጠም አደጋ የሚታደጉ የባሕር ላይ ነፍስ አድን ድርጅቶች የማንቂያ ደውሉን እያሰሙ ነው ። በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች በዓለም ላይ ካሉ አደገኛ የስደት መስመሮች አንዱ የሆነውን የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው እየፈለሱ ነው ። በባሕር ከመስጠም ከተረፉት መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።
አምስት ጊዜ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረው ባይሳካላቸውም ራይላ ኦዲንጋ የኬንያን ዴሞክራሲ እና ምርጫ የይስሙላ እንዳሆን ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል። በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦዲንጋ በተቃዋሚነታቸው ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ ተሰደዋል። ግን እስከ መጨረሻው አላፈገፈጉም። በማዳጋስካር ጦር ሠራዊት ውስጥ ካፕሳት ተብሎ የሚጠራው ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ሚካኤል ራንጄሬሪና ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። የ51 ዓመቱ የጦር መኮንን ሥልጣን የጨበጡት ለሦስት ሣምንታት ከተካሔደ የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጄሊና ከሥልጣን ተባረው ነው።
ፎኩም «በምርጫው ቀን ለመምረጥ መውጣት መቻላችንን መጠየቅ ጀምሬያለሁ፣ሁሉ ነገር ከተዘጋጋ ድምጽ ለመስጠት ወደምርጫ ጣቢያ እንዴት እንሄዳለን» ይላሉ።«የመራጮች ቁጥር በፀጥታ እጦት ካነሰ ምርጫው የተሀድሶ መንገድ ሳይሆን “የይስሙላ” ነው የሚለውን ግንዛቤ ያጠናክራል ፤መራጮች እንቅፋቶችን ከተቃወሙ ግን ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።»
የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ ተጨምሮበት ደቡብ ሱዳንን እንደገና ወደ ግጭት ሊመልሳት ይችላል እየተባለ ነው። ለዛም ነው የሪክ ማቻር የፍርድ ሂደት የእሳቸውና እና የተባባሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የደቡብ ሱዳን የወደፊት እጣ ፈንታን የሚወስን ነው የሚባለው።
የማሊ፣ ኒጀር እና የቡርኪናፋሶ መንግሥታ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተገረሱ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተመሰረተዉ የሳህል ግዛቶች ህብረት (AES) በያዘዉ ያልተሟሉ ግቦች እና የኢኮኖሚ ተስፋዎች ብሎም ሚዛናዊ ያልሆኑ ጥቅሞች በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ትችቶች ገጥሞታል። ህብረቱ ዛሬ እስከ ምን ድርሶ ይሆን?
ደቡብ ሱዳን አዲስ የእርስ በርስ ግጭት አፋፍ ላይ ያለች ይመስላል። ከጎርጎረሳዉያኑ 2018 ጀምሮ በሃገሪቱ የነበረዉን ከፍተኛ የእርስ በእርስ ጦርነት ያስቆመዉ የሰላም ስምምነት በተለይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በአገር ክህደት እና በሌሎች ወንጀሎች ከተከሰሱ እና እስር ላይ ከዋሉ በኋላ የሰላም ስምምነቱ ዳመና ያጠላበት ይመስላል።
የኬንያ ፕሬዝዳንት የፓርላማ አባላቱን ጉቦ እየተቀበሉ ነው ብለው በጅምላ ከወቀሱ ወዲህ፤ የኬንያን ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ነው። በሀገሪቱ የተደረገ አዲስ ጥናት እንዳመለከተው ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቻ ጎቦ ለመስጠት ይገደዳሉ። በኬንያ በየዓመቱ ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከዝርፊያ እና ከህገወጥ የገንዘብ ፍሰት እንሚጠፋ ይገመታል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል።
የኮቪድ-19 ዓለምን ካመሰ በኋላ የተሠሩ ክትባቶች በፍጥነት እና በፍትኃዊነት አለመዳረሳቸው የአፍሪካን ጥገኝነት አጋልጦታል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ አፍሪካ ክትባቶች እና መድሐኒቶች በማምረት ከጥገኝነት እንድትላቀቅ በርካታ ዕቅዶች አሉ። ዕቅዶቹ በረዥም ጊዜ ምን ያክል ዘላቂ ናቸው?
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል። የኮቪድ-19 ዓለምን ካመሰ በኋላ የተሠሩ ክትባቶች በፍጥነት እና በፍትኃዊነት አለመዳረሳቸው የአፍሪካን ጥገኝነት አጋልጦታል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ አፍሪካ ክትባቶች እና መድሐኒቶች በማምረት ከጥገኝነት እንድትላቀቅ በርካታ ዕቅዶች አሉ። ዕቅዶቹ በረዥም ጊዜ ምን ያክል ዘላቂ ናቸው?
ለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ እና ለፖሊስ የጭካኔ ጥቃት የተጋለጡ ኬንያዉያን ተቃዋሚዎች ለከፋ የአዕምሮ መታወክ እየተጋለጡ ነው። ጠበቅ ያለ የሳይበር ደህንነት ህግን ተግባራዊ ያደረጉት የዛምብያው ፕሬዚዳንት በድጋፍ እና ተቃዉሞ መሃል ናቸው
loading
Comments 
loading